Ring ring
free book gift

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።


Iqra

=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=

ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ


1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።

2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።

3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።

4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
Iqra
Iqra

Homeየወጣቱ ተልዕኮ ምንነትየአቂዳ ትምህርቶችየሶላት መመሪያረመዷንሙስሊም ሴቶችኢስላማዊ ቤተሰብከታሪክ ማህደርሐዲስለወጣቶችትምህርትና መሰረታዊ ክህሎታችጤናችንግጥምጥያቄና መልስኢስላማዊ መዝገበ ቃላት
free book gift

=<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=

ያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም አንብብ!

free book gift

በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።

free book gift

Tumblr milowfVMSa1reybgso1 500

ሁለት በአደን(የበረሀ እንስሳት) በመያዝ እሚተዳደሩ ሰዎች ነበሩ። ሁለቱም ለዘመናት ያህል አብረዉ ይሰሩና አበረው ይኖሩ ነበር። ነገር ግን አንደኛው ከአማኞች ሲሆን ሌላኛው ግን ከእምነት ወጪ ነበር።

ከእለታት አንድ ቀን አደን ላይ ዉለዉ አንድ ቦታ ላይ ለዕረፈት ተቀምጠው ጠመንጃቸወን(መሳርያቸዉን) እየወለወሉ(እያጸዱ) እያለ መሳርያዉ ድንገት ይፈነዳና ከእመነት ዉጪ የሆነውን ሰዉ ጣት ትቆርጠዋለች። በዛ ጉዳት የደረሰበት ሰዉ አሞት ብዙ ሲጮህ ያ ጓደኛው አይዞህ ለኸይር ይሆናል ይለዋል። በዛ ንግግር የተቆጣው ተጎጂ እንዴት ለኸይር ነው ትላለህ? እጄን መቆረጤ አሰደስቶሀልን? በማለት ይዞ በአንድ ቤት አስሮ አስቀመጠዉ።

አደንም ለብቻው ሆኖ ማደን ጀመር። እዛ አካባቢ በጣም ጫካ በመሆኑ ሰው ሚባል ማየት ብርቅ ነዉ። ግን እዛ አካባቢ ሰዎች በዓመት አንዴ እየመጡ የሚገዙት ጣኦት አለ። ጣኦታቸዉን የሚገዙት በየአመቱ ሰዉን እያረዱ ነበረ ሚያከበሩትና ለዚህ አመታዊ በዓላቸው የሚያርዱትን ሰዉ እያደኑ(እያፈላለጉ) ሳለ ለዚህ ብቻውን እንስሳትን የሚያድነዉን ያገኙታል። ይዞዉም የእርድ ስነ-ስርዓት ወደ ሚፈፀምበት ቦታ ይወስዱታል። ታድያ ለእርድ በተዘጋጀበት ሰዓት ነበር ጣቱ እንደተቆረጠ ያወቁት። ይህንን ሲያዉቁ አካለ ጎደሎ እንዴት ለአምላካችን እናርዳለን በማለት ይለቁት እና በምትኩ ሌላ ያፈላልጉ ጀመር።

ሱብሃነሏህ! የዛኔ ነበር ያ ሙእሚን ጓደኛው እጅህ መቆረጥህ ለኸይር ያለዉን ትክክል መሆኑን የገባው። ወዲያው አስሮ ወዳስቀመጠበት ቤት ይሄድና ይፈተዋል። ስለ ገጠመዉ ሁኔታ ይነግረዉ እና በእሱ ላይ ላደረሰበት የተሳሳተ ቅጣት ይቅርታ ይለዋል። አሁንም ግን ያ ኢማን ያለዉ ሰዉ በድጋሚ እንዲህ ይለዋል፦ የኔ መታሰርም እኮ ለኸይር ነው ይለዋል። በንግግሩ በመገረም ያንተ መታሰር ደሞ ምን ኸይር አለዉ? ብሎ ጠየቀዉ። አንተን ለማረድ ይዘዉህ ነበር፤ አካለ ጎደሎ ብለው ሲለቁህ አብሬህ ብኖር እኔን ነበር የሚያርዱኝ። ስለዚህ እስር ላይ መቆየቴ ለኸይር ነው አለዉ።

ሱብሃነ አሏህ!
ሱብሃነ አሏህ!
ሱብሃነ አሏህ!!!

By Amira muhammad member of Youth-Mission

ይህን ፔጅ ላይክ ያድርጉ
♥Youth-Mission የወጣቱ ተልእኮ♥
page:
http://facebook.com/youth.mission29

'~'-.,__,.-'~'
_,.-'~''~'-.,_


1081

የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
free book gift

Download Islamic Books
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ

Important Web Links


free book gift

free book gift

free book gift

ስለወጣቱ ተልዕኮ ምንነት ለማወቅ እዚህ ላይ ክሊክ ያድርጉ

Copyright©Youth-Mission የወጣቱ ተልዕኮ